top of page
Search

ሰበር ዜና !

1 hour ago
1 min read

ትዮ ሰገነት ሚዲያ


መስከረም፦ 13/ 2019ዓ/ም



ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ላሊበላ አየር ማረፊያ ለማረፍ በመጓዝ ላይ የነበሩ ሁለት ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ላይ ተኩስ ተከፍቶ አንደኛዋ ከጥቅም ውጭ ስትሆን ሌላኛው ደግሞ የበረራ አቅጣጫዋን ቀይራ የአመራር ስምሪት እንዲሁም ድጋፍ ሳትሰጥ ወደመጣችበት ተመልሳለች።



ሄሊኮፕተሮቹ ለማረፍ ወደ ቀጭን አበባ በተጠጉበት ወቅት በፋኖ በሜካናይዝድና ዘመናዊ መሳሪያወች ተኩስ የተከፈተባቸው ሲሆን፣ አንደኛዋ ሄሊኮፕተር በተሰነዘረበት ጥቃት ከጥቅም ውጭ ስትሆን ሁለተኛዋ ሄሊኮፕተር ደግሞ እንዳረፈች ወዲያውኑ አቅጣጫዋን በመቀየር በግራር አምባ በኩል ወደ መጣችበት ተመልሳለች።



በውስጥ በተደረገ ማጣራት በሄሊኮፕተሮቹ ጄኔራል ተስፋዬ እና አንድ ሚኒስትር ተሳፍረው እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ ጥቃቱ በምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር፣ በ81ኛ ውባንተ አባተ እና በራስ አንችም ክፍለጦር የተናበበ ኦፕሬሽን በሄሊኮፕተሮች እና በአመራሮቹ ላይ ጉዳት ሊደርስ ችሏል።



በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት ረፋድ አካባቢ በተለምዶ ደጎሳች አካባቢ በደረሰ ፍንዳታ በፒካፕ ቶዮታ ተሽከርካሪ ሲጓዙ የነበሩ የላስታ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ኃላፊ ኢንስፔክተር ወዳጅ ሲደመሰሱ፣ የወረዳው ደህንነት ባለሙያ አቶ ሰማኝ አበበ እና የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኢንስፔክተር መቆያ ጣሰው በከባድ ሁኔታ መቁሰላቸው የ13ኛ ኮር ቃል አቀባይ መረጃዉን አድርሶናል።



ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ


መስከረም፦ 13/ 2019ዓ/ም

 
 
 

Recent Posts

See All
ሰበር ዜና!

የዐብይ ሰራዊት ተደመሰሰ ! -- ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር በተዉጣጡ ወስን ኃይሎች በርካታ የጠላት ኋይል ሲደመሰስ፤ ቁጥሩ ያልታወቀ ሞርታር፣ዲሽቃወችን ጨምሮ ለቁጥር እሚያዳግት መሳሪያዎችን ገቢ ማድረግ ተችሏል! አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር በእ

 
 
 
ሰበር ዜና !

በአፋር ክልል ስድስት ወረዳዎች ነጻ ወጡ ! መስከራም 13 ቀን 2019 ዓ/ም ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ አረመኔው የዐብይ አህመድ አገዛዝ በአፋር ክልል ከሌሊት ጀምሮ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ውጊያ በርካታ ሰራዊቱ ተደምስሶና ተማርኮ 6 የአፋር ወረዳዎች የትብብሩ አካል በሆነው በአፋር ኡጉጉሙ ቁጥጥር ስር

 
 
 
ሰበር ዜና !

በማረሚያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች '' ለወታደራዊ ዘመቻ እንዲሰለፉ'' እየተገደዱ መሆኑ ተገለፀ! ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ በደቡብ ወሎ ዞን በደሴ ከተማ በሚገኘው ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙና ከዚህ በፊት መከላከያ ፣ ልዩሀይልና በሌሎች ወታደራዊ ዘርፎች ተሰማርተው ያገለግላሉ የነበሩ ታራሚዎች ብቻ ተመርጠው '' ለወታደራዊ ግ

 
 
 

Comments


bottom of page