ዝርዝር መረጃውን ያንብቡ ለሌሎችም ያጋሩ ።
- ethiosegenetmedia

- 4 days ago
- 3 min read





-----
ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ
ታህሳስ 8/2018 ዓ/ም
በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ም/ችሎት የታህሳስ 8/2018 የችሎት ውሎ መረጃ !
አማራነትን እንደ ወንጀል በቆጠረው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ በተለያዩ መዝገቦች በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ፍ/ቤት ቀርበዋል።
(1) ~ በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው ፦
በሕመም ምክንያት እየተገኘ ካልሆነው ከአማረ መለሰ በስተቀር የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌውን ጨምሮ 15 ተከሳሾች በችሎት ተገኝተዋል።
መዝገቡ የተቀጠረው ከመጋረጃ ጀርባ ይመስክር የተባለውን "ይታያል በሩቁ" የተባለውን ምስክር ለመስማት ነው።
ይህ ምስክር በግልጽ ችሎት ቀርቦ ሊመሰክር ይገባል በሚል የተከሳሾች ጠበቆች ጉዳዩን እስከ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና ሰበር ሰሚ ችሎት ቢወስዱትም ይግባኙ ውድቅ ተደርጎ ነው ይመስክር የተባለው።
በዚህም መሰረት በእለቱ ከመጋረጃ በስተጀርባ የሚከናወነውን የምስክር ሂደት ለመከታተል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ እና የተከበሩ አበባው ደሳለው እንዲሁም የአማራ ክልል እና የፌደሬሽን የም/ቤት አባል የተከበሩ ሀብታሙን ጨምሮ የተከሳሾች ቤተሰቦች እና ሌሎች የችሎት ታዳሚዎች በችሎት ተገኝተዋል።
ምስክሩ ከመሰማቱ በፊት በጠበቆች በኩል ችሎቱ ምስክሩ ስለመቅረቡ በዐይኑ ተመልክቶ ሊያረጋግጥ እና ዐቃቤ ሕግም ሆነ ሌላ አካል አብሮት እንዳይቀመጥ ይልቁንስ ከአጠገቡ አንድ ዳኛ ተቀምጦ ሊከታተል ይገባል ፤
ዘመኑ የቴክኖሎጅ የAI ጊዜ በመሆኑ ምስክሩ ፊት ለፊት ሳይቀርብ ከርቀት ሆኖ ላለመመስከሩ ፍ/ቤት በምን ያረጋግጣል ?
ምስክሩ ከበስተጀርባ ስለመኖሩ በምን እናውቃለን ?
ቃለ መሀላስ እንዴት ይፈጽማል ? የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
በተመሳሳይ የተከበሩ ክርስቲያን ታደለ ሲቀጥሉ ምስክሩ ትክክለኛ እና ቃሉም የራሱም ስለመሆኑ እንዴትስ ይታወቃል ?
ተጽፎ ተሰጥቶት እያነበበ ላለመሆኑ እንዴት ይታወቃል ? ከፍ ሲል ደግሞ ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ራሱ ምስክር ሆኖ ላለመቅረቡ በምን እናውቃለን ? ሲሉ ምስክሩ በእውነት ከመጋረጃመኖሩ እንዲረጋገጥ ጠይቀዋል።
ይህን ቅድመ ምስክር የመብት ጥያቄን ተከትሎ በችሎት ተሰይመው የነበሩት ሶስቱም ዳኞች ~ ፈይሳ በዳዳ (መሀል ዳኛ) ፣ ጌትነት መዲና (የግራ ዳኛ) እና አስራት እሸቱ (የቀኝ ዳኛ) ከችሎት ወጥተው ለ2 ሰዓት ገዳማ ከቆዩ በኋላ ተመልሰው በችሎት ተሰይመዋል።
የተከሳሾች ጠበቆች እና ዐቃቤ ሕግ ባህሩ ይፍሩ እና አዲሱ ግዛውም ቀርበዋል።
እንደተሰየሙም ምስክሩ መምጣቱን አረጋግጠናል ፤ የቀኝ ዳኛ አስራት እሸቱ ደግሞ ከጎኑ ተቀምጠው ሂደቱን የሚከታተሉ ይሆናል ፤ ሂደቱ ግን ከቀኑ 7 ሰዓት ይቀጥላል በማለት የምሳ ሰዓትም ደርሶ ስለነበር ከተሰየሙበት ችሎት ተነስተዋል።
ከሰዓት በኋላም እንዳሉት ሳይሆን ከቀኑ 8: 20 ነው ተሰይመው ምስክሩን መስማት የተጀመረው።
ዐቃቤ ሕግ ከአሁን ቀደም ምስክሩ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ያስረዱልኛል ብለው ነበር።
በእለቱ ግን የተናገሩት በተከበሩ ክርስቲያን ታደለ ላይ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
ምስክሩም የተከበሩ ክርስቲያን ታደለ ለጎጃም ፋኖ ስር ገረመው ወንድ አወክ ብርጌድ ለሻለቃ 2 መሪ ስልክ ደውለው "አይዟችሁ" በሚል ስለማበረታታቸው አንድ አባል ነግሮናል ፤ "ነገር ግን መች እንደደወሉ አላወኩም" ሲል የስሚ ስሚ ቃሉን ተናግሯል።
አባሉ ይህን የነገረን ሀምሌ 7/2015 ጎጃም መከላከያ ትጥቅ ሊያስፈታ መጥቷል በመባሉ ጦርነት ገጥመን ከሰነበትን በኋላ ከቀኑ 11 ሰዓት እረፍት ላይ እያን ነው ሲል አውስቷል።
ይህን ተከትሎ በጠበቆች በኩል መስቀለኛ ጥያቄዎች ፣ በዐቃቤ ሕግ ድጋሜ ጥያቄዎች እንዲሁም በዳኞች በኩል የማጣሪያ ጥያቄዎች ቀርቦለት ምስክሩም ምላሽ ሰጥቷል።
ችሎትም ተከሳሾች የሰነድ ማስረጃ አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ ሲል ለጥር 8/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የቂሊንጦ ማ/ቤት ተከሳሾች በዐቃቤ ሕግ የሚሰጣቸውን ሲዲ እንዲያዳምጡ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥር ታዟል።
ተጨማሪ መረጃ የምናጋራ ይሆናል።
(2)~ ሰይፈ ወይንሸት ማሞ ፦
ሰይፈ ወይንሸት ማሞ ኸአሁን ቀደም ከሌሎች አባሪዎች ጋር በሽብር ወንጀል ተከሶ የክስ ሂደቱን በቂሊንጦ ማ/ቤት በእስር ላይ ሆኖ እየተከታተለ ቢሆንም ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ አሁንም ተጨማሪ ክስ የመሰረተበት መሆኑ ታውቋል።
በእለቱም አዲስ እና ተጨማሪ የተባለው ክስ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ተሰጥቶታል።
የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ አማራነትን እንደ ወንጀል በመቁጠር በአዋጅም ሆነ ያለ አዋጅ በጅምላ ግድያን ፣ ማፈናቀልና በሰው ሰራሽ ርሃብ ማሰቃየትን ጨምሮ እስርን በተደራጀ መልኩ እየፈፀመ መሆኑ ይታወቃል።
(3)~ ገዛኽኝ ጥላሁን ታምራት ፦
ለወራት በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ በእስር ላይ የቆየውና በቅርቡ ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት የወረደው ገዛኽኝ ጥላሁን ታምራት የተመሰረተበትን የሽብር ክስ በማ/ቤት ሆኖ ሂደቱን እየተከታተለ መሆኑ ይታወቃል።
ተከሳሹ ታህሳስ 8/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርቦ ነበር ፤ ቀጠሮውም ሕዳር 26/2018 የተደረገውን የዋስትና ክርክር መርምሮ ችሎቱ ብይን እሰጣለሁ ማለቱን ተከትሎ ነው።
ዘገባውን ያድረሰን አውሎግስ ነው።
ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ
ታህሳስ 8/2018)




Comments