top of page
Search

ዐበይት ዜና !


ree
ree

---------

በመርሀቤቴ ቀጠና የአፄ አምደ ጽዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦር ከአገዛዙ ሀይል ጋር ታላቅ ተጋድሎ ሲያደርግ፤ ንጉስ ታዬ የተባለ የብልፅግናው ሚላሻ አጎቱን ጨምሮ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላትን በጭካኔ መግደሉ ተሰማ።

ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

ታህሳስ 8/2018 ዓ/ም


የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦር 3ኛ ቀስተ ንህብ ሻለቃ በመርሀቤቴ ሚዳና ሬማ ወረዳ በይጎቪያ ጎባቢት ቀበሌ ልዩ ቦታው በበርና ቦዴ ተራሮች ላይ ከብልፅግናው የ101ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ጋር የተቀናጀ ውጊያ እያደረጉ መሆኑን የክፍለጦሩ ም/የህ/ግ/ክፍል ኃላፊ ፋኖ ዲ/ን ያሬድ ታመነ መረጃውን ከግንባር አድርሷል።


እስካሁን በተካሔደው ውጊያ ከ11 በላይ የሞርተር ጥቃቶች በአገዛዙ ሰራዊት በግደለሽነት መተኮሳቸውን ተከትሎ በአርሶ አደሩ የደረሰ አዝመራ ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።


በሌላ በኩል በመርሀቤቴ አውራጃ በተፈፀመ አሳዛኝ ግዲያ ሶስት (3) የአንድ ቤተሰብ አባላት በብልግናው የሚላሻ አባል በግፍ መገደላቸው ተሰምቷል።


ትላንት ታህሳስ 07 ቀን 2ዐ18ዓ.ም ጨለማን ተገን በማድረግ ከምሽቱ 3:00 ላይ በመርሀቤቴ አውራጃ የግሬት ቀበሌ ዞማ ጎጥ ነዋሪ በሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ በብልፅግናው ገዳይ ኃይል ይሁንታ በተፈፀመው እጅግ ዘግናኝ ግድያ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት አቶ ንጉስ ታዬ በተባለ የሚሊሻ አባል በግፍ ተገድለዋል።


ሚሊሻው የእናቱን ወንድም የ3 ልጆች አባት አጎቱን አቶ ሀብታሙ ብርሌው ፣ የአጎቱን ሚስት ወ/ሮ ምስወይ ወርቄ እና የ8 ዓመት ህፃን ልጃቸውን ህፃን ሚጥወይን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድል የመከላከያው ካምፕ ውስጥ መደበቂያ ማድረጉን ተረጋግጧል።

 
 
 

Recent Posts

See All
ዐበይት ዜና !

ዐበይት ዜና ! ------------ የፋኖ ኃይሎች በጎጃም ወሳኟን ከተማ ተቆጣጥረው ውለዋል፤ በወሎ ቤተ አማራ የውጊያ ቀጠናዎች ደግሞ ከደሴ ዙሪያ ወረዳ እስከ ደላንታ ከባድ ትንቅንቆች ተካሂደዋል፡፡ ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ ህዳር 7/2018 ዓ/ም የሻለቃ አመራሩን ጨምሮ በርካታ የአገዛዙ ጦር አባላት ሙትና

 
 
 

Comments


bottom of page