top of page
Search

ዐበይት ዜና !

ዐበይት ዜና !

------------

የፋኖ ኃይሎች በጎጃም ወሳኟን ከተማ ተቆጣጥረው ውለዋል፤ በወሎ ቤተ አማራ የውጊያ ቀጠናዎች ደግሞ ከደሴ ዙሪያ ወረዳ እስከ ደላንታ ከባድ ትንቅንቆች ተካሂደዋል፡፡


ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

ህዳር 7/2018 ዓ/ም


የሻለቃ አመራሩን ጨምሮ በርካታ የአገዛዙ ጦር አባላት ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል፡፡



የአፋብኃ ቴድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር የምስራቅ ጎጃሟን ደብረወርቅ ከተማ፣ ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን ከንጋት 11 ሰዓት ጀምሮ በ5 የተለያዩ አቅጣጫዎች ውጊያው በመክፈት ተቆጣጥሮ መዋሉ ተሰምቷል፡፡


የፋኖ ኃይሎች ተቆጣጥረዋት የዋሉት ደብረወርቅ ከተማ፣ ውጊያው በወርቁ ማደያ፣ በፖሊስ ጣቢያው ፣ በጠዛ ወንዝ፣ በአዲሱ ገበያ እና በቴክኒክ በኩል ሙሉ ከበባ በማድረግ እንደጀመረ ከግንባር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡


የደብረወርቅ ፖሊስ ጣቢያን ጨምሮ ሙሉ ከተማዋን ለ6:00 ሰዓታት ተቆጣጥረው የቆዩት የፋኖ ኃይሎች፣ በፖሊስ ጣቢያው የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል ታስረው የነበሩ ከ100 በላይ የግፍ እስረኞችን ነጻ ሲያወጡ፤ በአጠቃላይ ውጊያው በርካታ ወታደራዊ ቁሳዊ ምርኮ እንደቀናው ገልጾል፡፡ 


27 ክላሽንኮቭ፣ 1650 የክላሽ ተተኳሽ እና 29 የወገብ ትጥቆችን ገቢ ማድረጉ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ በግንባር መረጃው ይፋ አድርጓል፡፡


በሌላ አውደ ውጊያ ስናን አባጅሜ ሻለቃ በደፈጣ ጥቃት በአገዛዙ ጦር ላይ ጉዳት ማድረሱ ተሰምቷል፡፡


አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር በምዕራብ ጎጃም ዞን ስናን ረቡዕ ገበያ ከተማ በከፈተው ማጥቃት በቁጥር ያልገለጸው ቁሳዊ እና ሰዋዊ ጉዳት ማድረሱን አሳውል፡፡


በዚሁ ውጊያ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች በምርኮ መገኘቱንም ዕዙ ገልፆል፡፡


በሌላ የግንባር መረጃ፣ በወሎ ቤተ አማራ የተለያዩ ቀጠናዎች ውጊያዎች ቀጥለው መዋላቸው ተሰምቷል፡፡


ደላንታ ዙሪያ በአገዛዙ ሰራዊት የሻለቃ አመራር ጥቃት ሲፈፀምበት፤ ከ10 በላይ የሚሆኑ እግረኛ ሰራዊት ደግሞ ሙትና ቁስለኛ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡


አፋብኃ ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር  በአገዛዙ የሻለቃ አመራር ላይ በሰነዘረው ማጥቃት ከባድ ቁስለኛ ማድረጉን  ከሁለት ቲም በላይ እግረኛ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ማድረግ መቻሉን ዕዙ በግንባር መረጃው አረጋግጧል፡፡


ዚሃ ላይ በልጅ እያሱ ኮር የፋኖ ኃይሎች በዋለው ውጊያ ክፉኛ ሲመታ ወደ ደላንታ ወረዳ የሸሸው የአገዛዙ ጦር፣ በፅናት ክፍለ ጦር መክት ሻለቃ 3ኛ ሻምበል የደፈጣ ጥቃት ተፈጽሞበት ተጨማሪ ጉዳት ማስተናገዱን የግንባር መረጃው ላይ ተመላክቷል፡፡

አምባሰል ወረዳ ውስጥ ባትሪ በተባለ ቦታ ላይ በተደረገ ደፈጣ ሻለቃ መሪው ከባድ ቁስለኛ መሆኑን፤  ሰባቱ ደግሞ እንደሞቱ፤ አስራ አራቱ ከባድ ቁስለኛ መሆናቸውን አፋብኃ በግንባር መረጃው አረጋግጧል፡፡


በሌላ መረጃ፣ ምኒልክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ደሴ ዙሪያ ለአንድ ሳምንት ተከታታይ በተደረገ ተጋድሎ በርካታ ድሎችን ማስመዝገቡን ዕዙ ገልጾል፡፡  


በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም ደሴ ዙሪያ ለአንድ ሳምንት ተከታታይ መደበኛ ውጊያ በማድረግ ነጻ ቀጠናውን ከማስፋቱም በላይ በአገዛዙ ጦር ላይ ከባድ የተባለ ኪሳራ ማድረሱ ታውቋል፡፡


የፋኖ ኃይሎች በደሴ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ በርከት ያሉ ቀበሌዎችን በመቆጣጠር የህዝብ አስተዳደር መዋቅር መዝረጋታቸውም በግንባር መረጃው ላይ ተመላክቷል፡፡


ኢትዮ ስገነት ሚዲያ

ህዳር 7/2028 ዓ/ም

 
 
 

Comments


bottom of page