top of page
Search

ሰበር የድል ዜና ከሸዋ ሮቢት !

ጀግናው ራንቦ ክፍለጦር በሸዋ ሮቢት ከተማ በ103ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ የተሳካ የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽኝ ማድረጉን ክፍለጦሩ አስታወቀ።


   ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

መስከረም 29 ቅን 2018


ሰሞኑን በሁሉም የሸዋ ቀጣና የጀመረው በአይነቱ ለየት ያለ የተቀናጀ አውደ ውጊያው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2018ዓ.ም ከለሊቱ 10:00 ጀምሮ የአፄ አምደ ጽዮን ኮር አካል የሆነው ጀግናው ራንቦ ክፍለጦር በርካታ መሽጎችን በመስበር በሸዋ ሮቢት ከተማ ልዩ የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን ማድረጉን የክፍለጦሩ የህ/ግ/ክፍል ሃላፊው አስታወቀ።


የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት(አፋሕድ) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር በታላቁ አርበኛ ስንታየሁ ማሞ ስም የተሰየመው ጀግናው ራንቦ ክፍለጦር በአገዛዙ የ103ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ በድቅድቅ ጨለማ በሁለት አቅጣጫ ተስበው በመግባት ከለሊቱ 10:00 ጀምሮ የተቀናጀ ጥቃት ፈፅሟለ።


ጀግኖቹ የራንቦ አናብስቶች በአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሃላል በሁለት አቅጣጫ ወደ ከተማው ዘልቀው የገቡ ሲሆን በእቦሬ ተራራ እና መርየ በተባለ አቅጣጫ በመሸገበት ካምፕ ድረስ ዘልቀው በመግባት ክፍለጦሩ በወሰደው ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት በምሽግ ላይ የነበረውን በርካታ የአገዛዙ ወራሪ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ የደመሰሰ ሲሆን፣ በህይዎት የተረፈው የጓዱን አስክሬን ጥሎ ሲሸሽ፣ በተለምዶ ምርጥ 50 ተብሎ የሚጠራው የሚሊሻ ስብስብ ከተደበቁበት መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ውስጥ ወጥተው መፈርጠጣቸውን ክፍለጦሩ አስታውቃለ።


የክፍለጦሩ የቃኝ ፋኖ ሰራዊት ከሻለቆች ጋር ባደረጉት ከፍተኛ መናበብ በቀይ ቦኔት ለባሹ የ103ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ እና የጥምር ጦሩ ስብስብ ላይ በተወሰደው መብረቃዊ ጥቃት ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል።


የአማራው ባንዳ ተብሎ የሚጠራው ለሆዱ ያደረ የሚሊሻ ስብስብ የጓዱን አስክሬን እና ከሞት የተረፈውን ቁስለኛ እየጣለ እግሬ አውጪኝ ብሎ ሲፈረጥጥ የነፍስ ወከፍ መሳሪያና ወታደራዊ አልባሳትን ጨምሮ በርካታ ሰነዶች በምርኮ ገቢ ሆነዋል።


ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በተገኘው መታወቂያ መሰረት ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው የመከላከያ አመራሮች በጀግናው ራንቦ ክፍለጦር በተወሰደባቸው መብረቃዊ ጥቃት መደምሰሳቸው ተረጋግጧል።



  ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት‼️


         ድል ለአማራ ‼️


         ድል ለፋኖ ‼️


ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ !

መስከረም 29 ቀን 2018

ree

 
 
 

Comments


bottom of page