top of page
Search

ሰበር ዜና!

---

የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በጥምረት ጋሸና ከተማ በመግባት የአገዛዙ ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ጥቃት ፈጸሙ።

ታህሳስ 5/2018 ዓ/ም


አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ሰይድ ክፍለጦር እና ቀኛዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር ቃኞች ባደረጉት የጋራ ኦፕሬሽን በጋሸና ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እና ነዳጅ ማደያ ድረስ ዘልቀው በመግባት በርካታ የአገዛዙን ሰራዊት መደምሰሳቸው ታወቀ።


ታህሳስ 5/2018 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ በተደረገ የማጥቃት ኦፕሬሽን ሙሉ በሙሉ ውጤታማ በሆነ መልኩ ፋኖዎቹ ጋሸና መሀል ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እና ነዳጅ ማደያ አካባቢ ተሰብስቦ በነበረ የጥላት ሰራዊት ላይ ከባድ ጥቃት በመፈፀም ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱና ካድሬዎችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ ማድረሳቸውን የኢትዮ ሰገነት ሚዲያ የግንባር መረጃ ምንጮች አረጋገጡ።


ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰአት ሰዓት ጋሸና ላይ የሚገኙ አቡላንሶች የአገዛዙን ወታደር አስከሬንና ቁስለኛ በማጋዝ ወደ አቅራቢያ ሆስፒታል ሲያስገቡ እንደነበረ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል።


እንደ ምንጮቻችን መረጃ የፋሽስቱ ሰራዊት በከባድ መሳሪያ የታጀበ ተኩስን የከፈተ ቢሆንም ቅሉ በፋኖ ነበልባል ቃኝ ሻለቃዎች የአገዛዙ ሰራዊት ወደ መብራት ሃይል እንዲያፈገፍግ ተደርግጓል::


ይህ በእንዲህ እንዳለ የአገዛዙ ሰራዊት በውጊያው ሽንፈት ሲያስተናግድ መድፍና ዙ23 በግደለሽነት እያስወነጨፈ የተለመደ ንፁሃንን የመበቀል ተግባሩን እንደፈጸመም ታውቋል።


ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ


ታህሳስ 5/2018 ዓ.ም

 
 
 

Comments


bottom of page