ሰበር ዜና !
- ethiosegenetmedia

- Dec 14, 2025
- 1 min read

-----
የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የማኅበረ ቅዱሳን አባል በታጣቂዎች ተገደሉ።
ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ
ታኅሣሦ 5 ቀን 2018 ዓ.ም
የኅዳር ጽዮን ማርያምን በዓል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥር በምትገኘው በሐረቶ ማርያም በዓሉን አክብረው ሲመለሱ ሻንቡ ከተማ መዳረሻ ሲደርሱ የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ እና በርካታ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችና ወጣት የማኅበራት አገልጋዮች በሕገ ወጥ ታጣቂዎች መወሰዳቸው ይታወቃል።
ሌሎቹ ተፈትተው ቆይተው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ኡፋ እና የማህበረ ቅዱሳን አገልጋይ የሆኑት ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል::
ይህንን ኦርቶዶክሳዊያንን የማሳደድ ወንጀል ማህበረ ቅዱሳን በዘገባው ይፋ አድርጓል።
ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ
ታኅሣሦ 5 ቀን 2018 ዓ.ም




Comments