top of page
Search

ሰበር ዜና !



የደጀን ክፍለጦር በሌሊት ባደረጉት ተጋድሎ ድል ተጎናፀፈ

-

ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

ታህሳስ 3/2018


አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለጦር ታህሳስ 3/2018 ዓ/ም

ከሌሊቱ 11:30 እስከ 6:00 ሰዓት በዘለቀው ከባድ ፍልሚያ የጥላትን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወጊያውን በድል አድራጊነት እንደተወጣ የግንባር ምንጮቻችን አረጋገጡ።


በጋዞ ወረዳ ብር አፋፍ 01 ቀበሌ ላይ በተደረገ አውደ ውጊያ የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለጦር ፅናት ሻለቃና ኮማንዶ ሶስተኛ ሻለቃ ባደረጉት የማጥቃት ውጊያ በርካታ የጥላት ሰራዊት በመደምሰስ ምሽግ የተሰበረ ሲሆን ከጋሸናና ከአሁንተገኝ ከተማ በገፍ የመጣው የጥላት ሰራዊት ምሽጉን ለቅቆ ወደ መጣበት እግሬ አውጭኝ በማለት መፈርጠጡን ምንጮቻችን አያይዘው ግልጸዋል።


ደጀኖች በጠላት ላይ ባደረሱበት ከባድ ጥቃት የተደመሰሰ ሰራዊቱን በምሽጉ እየቀበረ የቀሩትን ሙትና ቁስለኛና በመኪና በመጫን ወደየመጣበት ተግተልትሎ መሸሹን ምንጮቻችን ለጣቢያችን አረጋግጠዋል።


እንደ ግንባር መረጃችን በውጊያው የተሳተፉት ይፋኖ ሻለቃዎች በተጠናከረ መልኩ ጠላት ላይ በወሰዱት እርምጃ ከሙትና ቁስለኛ ባሻገር በርካታ ተተኳሾችን መማረክ ተችሏል።


እንደ አቦሸማኔ ተወርውረው ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር የሚፋለሙት ፋኖዎች መዳረሻችን ድልና ነፃነት ነው። የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ! የሚል መፈክር ያሰሙ እንደነበረ የግንባር ምንጮቻችን በላኩት መረጃ አረግስግጠዋል።


ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

ታህሳስ 3/2018 ዓ.ም

 
 
 

Comments


bottom of page