top of page
Search

ሰበር ዜና !

Feb 19
1 min read

--

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን የምህረት አዋጅ በመቀበል ሥርዓቱን እየከዱ ያሉ የኦህዴድ መከላከያ ሰራዊት አባላት ቁጥራቸው ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መሄዱ አገዛዙን እያሸበረ መሆኑ ታወቀ።


የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ/ም

ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ


ዛሬም በማለዳው መነሻቸውን ከደራ ጉንዶመስቀል ከተማ ያደረጉት የአገዛዙ 15ኛ ክፍለጦር (ጋሻ ክፍለጦር) 5ኛ ሻለቃ የመከላከያ ሰራዊት ሁለት (2) የቲም መሪ አመራሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦር 3ኛ ቀስተ ንህብ ሻለቃን መቀላቀላቸውን ክፍለጦሩ በላከው መረጃ ገልጿል።


አፋብን ያወጣው የምህረት አዋጅ በበርካታ የሸዋ ከተሞች ከትሞ በሚገኘው የብልፅግናው አየር ወለድ እና እግረኛ ሰራዊት ተቀባይነት አግኝቶ በርካቶች ዕድሉን እየተጠቀሙበት መሆኑን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በህዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለኢትዮ ሰገነት ሚዲያ ገልፆአል።


  ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ/ም

 
 
 

Recent Posts

See All
ሰበር ዜና !

በማረሚያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች '' ለወታደራዊ ዘመቻ እንዲሰለፉ'' እየተገደዱ መሆኑ ተገለፀ! ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ በደቡብ ወሎ ዞን በደሴ ከተማ በሚገኘው ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙና ከዚህ በፊት መከላከያ ፣ ልዩሀይልና በሌሎች ወታደራዊ ዘርፎች ተሰማርተው ያገለግላሉ የነበሩ ታራሚዎች ብቻ ተመርጠው '' ለወታደራዊ ግ

 
 
 

Comments


bottom of page