ሰበር ዜና !
- ethiosegenetmedia

- Jan 28
- 2 min read
ሰበር ዜና !
---
ከወሎ ቤተአምሓራ የምኒሊክ ጥቃትን መቋቋም አቅቶት የቦታ ለውጥ በማድረግ ሸዋ መርሀቤቴ የገባው የ105ኛ አየር ወለድ ክፍለ በአፋብን ሸዋጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ ዳዊት ክፍለጣር ክፉኛ ተምርትቶ መበተኑ ተሰማ❗️
ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ
ጥር 18 ቀን 2018ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከተሰማራባቸው የሸዋ ቀጠናዎች ውስጥ በመርሀቤቴ አውራጃ በ105ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ በትላንትናው ዕለት ጥር 17 ቀን 2018ዓ.ም ድል ተቀዳጅቷል።
በሸዋ መርሀቤቴ አውራጃ ጠላት መነሻውን ከሬማ ከተማ በማድረግ በግብር ስም ህዝባችንን ለመዝረፍ በከተማዋ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው የመጅት ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ በመፈፀም ያልተመጣጠነ የግብር ተመን በመጣል በአስገዳጅ ገንዘብ እየሰበሰበ ባለበት ወቅት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር የጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር አካል የሆኑት በአስማረ ዳኜ 1ኛ ሻለቃ በተፈፀመው ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት ትላንት እሁድ ከቀኑ 6:00 ላይ የብልፅግናው አየር ወለድ አባላቱ ሙትና ቁስለኛ ሲሆን አንድ የሻምበል አመራሩ ተገድሏል፣ ከ8 በላይ የእጅ ስልካቸውን ሳይቀር ጥለው ሲሸሹ፣ ከ10 በላይ ወታደራዊ ቦርሳዎችንና ከህዝብ በመሰብሰብ ላይ የነበረ በርካታ ገንዘብና የጤና መድን ደረሰኝ እና ሌሎች ዶክመንቶችን በድንገት ጥለው ወደመጡበት ሬማ ከተማ እግሬ አውጭኝ ብለው መሸሻቸውን ኮሩ አረጋግጧል።
ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በሸዋ ይፋትና ጥሙጋ አውራጃ ኤፍራታና ግድም ወረዳ የአላላ እና የይምለዋ ቀበሌ ነዋሪዎች የሆኑት በርካታ ንፁሀኖች በብልፅግናው ካዲሬዎች ትዕዛዝ ሰጭነት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር የ7ለ70 ክፍለጦር አባላት እና በቀጠናው የሚገኙ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአርበኞች ጦር ሰራዊት አባላት የሆኑ ቤተሰቦችን የፋኖ ቤተሰብ በመሆናቸው ብቻ መርጠው በግፍ ማሰራቸውን ክፍለጦሩ አስታውቋል።
ከግፍ እስረኞቹ ውስጥ በከፊል:-
1. አቶ ሹመት ማናስቦ (የፋኖ መለስ ሹመት ወላጅ አባት)
2. ወ/ሮ አጁባን አየለ (የፋኖ አሳልፍ አጁባን ወለጅ እናት)
3. አቶ ሞገስ በቀለ (የፋኖ ይግረም ሞገስ ወላጅ አባት)
4. ወ/ሮ አሳበች መንገሻ (የፋኖ መመኪያ መሸሻ ወላጅ እናት)
5. ወ/ሮ አስናቁ ከስም (የፋኖ ተስፋዬ ከፈለኝ ባለቤት)
6. ወ/ሮ ብርቄ አለማየሁ (የፋኖ ነጋሽ ማሞ ባለቤት)
7. ወ/ሮ ብዙ በቀለ (የፋኖ ሀብቴ ዘነበ ባለቤት)
8. ወ/ሮ ብዙነሽ አስፋው (የአባት አርበኛ ቻሌ አስፋው እሕት)
9. አቶ ፋንታ ጌታቸው (የአባት አርበኛ ሞገስ ፋንታ ወላጅ አባት)
10. አቶ ወንድም አያሌው (የአባት አርበኛ ግዛቸው ወንድም ወላጅ አባት)
11. ወ/ሮ ወርቅነሽ በቀለ (የአባት አርበኛ አረጋኸኝ ማስረሻ ባለቤት)
12. ወ/ሮ ስንቅነሽ ዳኜ (የአባት አርበኛ በየነ ፋሩ ባለቤት)
13. ወ/ሮ አረጋሽ ንጋቱ (የአርበኛ ጋይስ ወዳጆ ባለቤት)
14. የአርበኛ መለሰ ገረመው ቤተሰብን ጨምሮ በርካታ የፋኖ ታጋይ ቤተሰቦች በአገዛዙ በአጣዬ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በግፍ ታስረው ይገኛሉ።
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ከግንባር መረጃዎችን አጠናቅሮ አድርሶናል።
ጥር 18 ቀን 2018 ዓ/ም
ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ




Comments