ሰበር ዜና !
- ethiosegenetmedia

- Dec 16, 2025
- 1 min read

---
የራንቦ ክፍለጦር በአገዛዙ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ ስኬታማ የደፈጣ ጥቃት ፈጸመ።
ኢትዮ ሰገነት ሚድያ
ታህሳስ 06/2018ዓ.ም
የጠላት መረጃ ገና ከዋዜማው ቀድሞ የደረሰው የፋኖ ሰራዊት ከጣርማበርና ደብረሲና ከተማ በመነሳት ወደ መዘዞ ከተማ ለማቅናት የሞከረውን ሰራዊት ከለሊቱ 10:00 ላይ የአፄ አምደ ጽዮን ኮር ራንቦ ክፍለጦር በልበላ ገብርኤል በተባለ ስፍራ በጣለው ደፈጣ የ104ኛ የአየር ወለድ ክፍለጦር ቃኝ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በክፍለጦሩ 2ኛ ነበልባል ሻለቃ ሲደመሰስ የመዘዞ ቀጠና የአርበኞች ጦር ሰራዊትም በውጊያው እየተሳተፉ እንደሚገኙ የግንባር የመረጃ አመልክቶአል።
በብልፅግናው አገዛዝ አዲሱ ዘመቻ መሰረት ዛሬ በሸዋ ቀጠና በሁለት ግንባሮች ውጊያ የከፈተ ሲሆን፣ ገና ከዋዜማው ያለ የሌለ ኃይሉን ከሸዋሮቢት እና ከደብረብርሀን ከተማ ተጨማሪ ሰራዊት ወደ ደብረሲና ከተማ በማስገባት ዛሬ ለሊት ጨለማን ተገን አድርጎ ወደ መዘዞ ከተማ ለማቅናት ባደረገው ሙከራ ከፍተኛ የደፈጣ ጥቃት የደረሰበት ሲሆን በሌላኛው ግንባር ከመንዝ ማማ ወረዳ ሞላሌ ከተማ የተነሳው የአየር ወለድና የጥምር ጦሩ ኃይል ወደ መለያና ባሽ ከተማ ሲንቀሳቀስ በራንቦ ክፍለጦር 3ኛ ማንበግር ሻለቃና በቀጠናው ከሚገኙ የአርበኞች ጦር ከባድ ጥቃት ማስተናገዱን ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል።
የራንቦ ክፍለጦር 2ኛ ነበልባል ሻለቃ በሰራው የተሳካ የደፈጣ ጥቃት አንድ አስገራሚ ልዩ ክስተት የታየ ሲሆን የብልግናው አየር ወለድ ክፍለጦር ለፈንጅ አምካኝ የሚጠቀምባት አነፍናፊ ውሻ ጭምር ከጠላት አስክሬን ጋር አብራ ተገድላ መገኘቷን ክፍለጦሩ አስታውቋል።
በሁለቱም አውደ ግንባሮች ውጊያው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ዝርዝር የተጠናቀረ የግንባር መረጃዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።




Comments