top of page
Search

ሰበር

ሰበር


የአፋብን ከራንቦ ክፍለጦርና ከ7ለ70 ክፍለጦር በተወጣጡ ውስን ሻለቆች በተደረገ የቅንጅት የጨበጣ ውጊያ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የአገዛዙ ሰራዊት ከጥቅም ውጭ ማድረጉን ኮሩ አረጋግጧል።



ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ


ሚያዚያ 07/2018ዓ.ም



ጠላት መነሻውን ከደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር፣ ከጉዶበረት እና ከቀይት ከተማ በማድረግ በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ስር በሚገኘው ወደ ባሶና ወረና ወረዳ ልዩ ቦታው አይዞሽ አሞራ በተባለ አካባቢ በሞርተርና ዙ-23 ታጅቦ በድሮን እየጨፈጨፈው የሚገኘውን የአማራ ህዝብ በኃይል የምርጫ ካርድ ለማሰራጨት ከንጋቱ 12:00 ላይ በማቅናት ላይ እያለ በጀግናው ሰራዊታችን በተፈፀመበት ጥቃት በርካታ የብልፅግናው ሰራዊት ከጥቅም ውጭ ሆኗል።



በደፈጣ ጥቃት የተጀመረው ውጊያ ወደ ጨበጣ ውጊያ ተቀይሮ የአማራ ፋኖ በአገዛዙ የቀይ ቦኔት ለባሽ ላይ በተጎናፀፈው ድል አገዛዙ በ2 አንቡላንሶች ሙትና ቁስለኛውን ወደ ደብረብርሀን ከተማ ሲያመላልስ ውሏል።



ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት እኩለ ቀን ድረስ በአይዞሽና አካባቢው አድማሱን ያሰፋው ውጊያ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ጠላት በደረሰበት ከፍተኛ ምት በመደናገጥ በዘፈቀደ ሞርተር ወደ ማህበረሰቡ እየተኮሰ ይገኛል።



በተመሳሳይ ዜና በትላንትናው ዕለት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአጼ ዘር ዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለጦር ከደብረብረሀን ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ ከኩኬለሽ እስከ በዞ ድርሰ በነበረው አውደ ውጊያ ክፉኛ የተመታው የጠላት ሀይል እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ ሙት እና ቁስለኛውን እየሰበሰበ፥ ናደው ክፍለጦር በመራቤቴ ቀጠና ባደረገው መጠነ ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ ክፉኛ የተመታው ጠላት የበቀል እርምጃውን ዛሬም በ107 እና ሞርታር ተራራዎችን እየደበደበ ይገኛል ሲል የአፄ ዘር ዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አስታውቋል።

 
 
 

Comments


bottom of page