top of page
Search

መረጃ

በመንዝ አውራጃ መንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ሀይማኖታዊ በዓላትን ለማወክ በተንቀሳቀሰው የ104ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ የተቀናጀ ጥቃት ተፈፀመ❗️


    ኢትዪ ሰገነት ሚዲያ

        ጥር 19 ቀን 2018ዓ.ም


በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝ አውራጃ በመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ በወገሬ ከተማ የከተመው የብልፅግናው ዙፋን አስጠባቂ ቅልብ ሰራዊት በዛሬው ዕለት ጥር 19 ቀን 2018ዓ.ም በህዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን የወይናባ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓልን ለማወክ ከለሊቱ 11:00 ላይ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር አካል የሆነው የምኒሊክ ክፍለጦርና በቀጠናው በሚገኙት በአርበኞች ጦር ሰራዊት በተጣለው የደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ መሆኑን ክፍለጦሩ አስታወቀ።


የወገን ሃይል ሶስት ስትራቴጅክ ቦታዎችን ቀድሞ የያዘ ሲሆን በጦስኝ ኮረብታ፣በአረቆ ሚካኤል እና በብረት ቀተራ ቦታዎች ላይ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ የተሳካ ጥቃት መፈፀሙን ኮሩ አረጋግጧል።


በደረሰበት ከፍተኛ ኪሳራ የተደናገጠው የአገዛዙ ዘራፊ ሰራዊት ተጨማሪ ሃይል ከመንዝ ማማ ወረዳ ሞላሌ ከተማ ወደ ወገሬ ከተማ በማጓጓዝ ላይ ሲሆን ይሕ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ውጊያው ተጠናክሮ መቀጠሉን ክፍለጦሩ በላከው የግንባር መረጃው አስታውቋል።


ዘገባው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።


ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

ጥር 19 ቀን 2018 ዓ/ም


 
 
 

Recent Posts

See All
ሰበር ዜና !

ሰበር ዜና ! ======= ደቡብ ጎንደር ዞን ሙሉ በሚባል ደረጃ በፋኖ እጅ ገብቷል ። ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ የካቲት ፩-፫ ፤ ፳፻፲፰ ዓ.ም ባለፉት ሶስት ቀናት በጎንደር እና ደቡብ ጎንደር ግንባሮች የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኙ ክፍለ ጦሮች ከአጋር ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የአገዛዙን ሰራዊ

 
 
 

Comments


bottom of page