ታሪክን የኋሊት !
- ethiosegenetmedia

- Dec 6, 2025
- 1 min read

------------
[አዲስ ፡ አበባ ፡ እንደፓሪስ ፡ ካልሆነች ፡ የሰው ፡ ደስታና ፡ ስራ ፡ ማየት ፡ ረዥም ፡ ህልም ፡ ማለት ፡ ነው ።]
∞ ∞ ∞
ቀኃሥ ንነ
ከምወድሽ ፡ ልጄ ፡ ልእልት ፡ ተናኘ ፡ ወርቅ ፡ ኃሥ ።
ጤናሽን ፡ እንደም ፡ ነሽ ።
እኛ ፡ ሥላሴ ፡ ይመስገን ፡ ደህና ፡ ነን ።
ተማርሴይና ፡ ተፓሪ ፡ የጻፍሽው ፡ ደርሷል ።
እሮብ ፡ ከምርምሩ ፡ በኋላ ፡ ሃኪሙ ፡ የሚለውን ፡ እጽፋለሁ ፡ ያልሽውን ፡ እንጠብቃለን ።
ስለኛ ፡ እረፍት ፡ እንድናገኝ ፡ የጻፍሽው ፡ ከልብ ፡ እንድትአስቢ ፡ አውቃለሁ ። ባይን ፡ የሚታየውን ፡ ለመለዋወጥ ፡ ካልሆነ ፡ አዲስ ፡ አበባ ፡ እንደፓሪስ ፡ ካልሆነች ፡ የሰው ፡ ደስታና ፡ ስራ ፡ ማየት ፡ ረዥም ፡ ህልም ፡ ማለት ፡ ነው ። አንዳንድ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ፎተግራፍ ፡ ያገኘሽ ፡ እንደሆን ፡ እንድትልኪ ።
ፒጃማ ፡ ፩ የሃር ፡ ፩ የጨርቅ ፡ ላይነት ፡ ጥሩ ፡ ከሚባለው ፡ ለኔ ፡ መጠን ፡ የሚሆን ፡ ገዝተሽ ፡ እንድትልኪ ። እግዚአብሔር ፡ ያሰብነውን ፡ ...
ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ !





Comments