top of page
Search

ሰበር ዜና !


----

በርካታ አዐብይ አህመድ ሰራዊቶች አገዛዙን በመክዳት ፋኖን ተቀላቀሉ !


       ኢትዮ ሰገነት ሚድያ !

       የካቲት 12 / 2018 ዓ.ም


የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በአገዛዙ ሃይሎች ላይ የተቀናጀ ጥቃት መፈፀሙን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት የአፄ አምደ ፂዮን ኮር አካል የሆነው አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር በመርሀቤቴ አውራጃ ሬማ ከተማ መሽጎ በሚገኘው የብልፅግናው ሰራዊት ላይ ወታደራዊ ኢላማ በማድረግ በከበባ ጥቃት ማድረሱን ክፍለ ጦሩ በላከው የግንባር መረጃው አስታውቋል።


ጠላት ከንጋቱ 12:00 ላይ መነሻውን ከሬማ ከተማ በማድረግ ወደ መጂት ቀበሌ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ልዩ ቦታው ቻይና ካምፕ በተባለ ስፍራ ላይ የጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር አካል የሆኑት በአስማረ ዳኜ 1ኛ ሻለቃ እና በቀስተ ንህብ 3ኛ ሻለቃ በተደረገበት ከበባ ለጊዜው ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የአገዛዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን ክፍለ ጦሩ ገልጿል።


የክፍለ ጦሩ ሻለቆች በሰሩት አስደማሚ የቅንጅት ኦፕሬሽን የጠላት ወታደሮች በውጊያ ወቅት የመፍረስ አደጋ ገጥሞት በመበታተኑ ከፍተኛ የዙ-23 ድብደባ ሽፋን በመስጠት የአለማችንን ፈጣኑ ሯጭ ዩሴን ቦልትን ያስናቀ ሩጫ በመሮጥ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ሬማ ከተማ መግባቱን ኮሩ በመረጃው አረጋግጧል።


ይሕ በእንዲሕ እንዳለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ በርካታ ወታደሮች ጥሪውን ተቀብለው ወደ ፋኖ እየገቡ ሲሆን፣ ሰሞኑን በርካታ የብልፅግናው ወታደሮች በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በየኮሮቹ ስር ባሉ የክፍለ ጦር አሀዶች ውስጥ በየቦታው ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ዕዙን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።


 

     ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

    የካቲት 12 / 2018 ዓ.ም

 
 
 

Comments


bottom of page