top of page
Search

ሰበር ዜና !

ሰበር ዜና !

=======

ደቡብ ጎንደር ዞን ሙሉ በሚባል ደረጃ በፋኖ እጅ ገብቷል ።


ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

የካቲት ፩-፫ ፤ ፳፻፲፰ ዓ.ም


ባለፉት ሶስት ቀናት በጎንደር እና ደቡብ ጎንደር ግንባሮች የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኙ ክፍለ ጦሮች ከአጋር ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የአገዛዙን ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ደማቅ ድሎችን አስመዝግበዋል።


፩. የስማዳ ወገዳና የሸረፍ ጎዴ ድል፦


በስማዳ ወረዳ "ወገዳ" ከተማና አካባቢው ለ24 ሰዓታት በተካሄደ ኦፕሬሽን፣ የጉና ክፍለ ጦር (እሥቴ ዴንሳ እና ሐገረ ቢዘን ብርጌዶች) የጠላትን የኮንክሪት ምሽጎች ሰባብረዋል።


• የጠላት ኪሳራ፦ 265 ተደምስሷል፣ 22 ተማርኳል።

• ምርኮ፦ 04 ብሬን፣ 01 ስናይፐር፣ 01 ዲሽቃ እና በርካታ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች።

• ውጤት፦ የወገዳ ከተማና ስትራቴጂካዊው የሸረፍ ጎዴ ተራራ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል።


፪. የመካነ ኢየሱስ እና "ዘመቻ መንግሥቱ ጥላሁን"


በጀግናው አርበኛ መንግሥቱ ጥላሁን ስም የተሰየመውና በእስቴ መካነ ኢየሱስ የተካሄደው የተቀናጀ ማጥቃት በአሸናፊነት ተጠናቋል። የጉና ክፍለ ጦር እና የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር በጋራ በመሆን ጠላትን እስከ ደብረ ታቦር አባርረዋል።


የተገኘ ድል፦


• መካነ ኢየሱስ ከተማ ከአገዛዙ ነጻ ሆናለች።

• 87 የፖለቲካ እስረኞች ከግዞት ተለቀዋል።

• ምርኮ፦ 05 ብሬን፣ 02 ስናይፐር፣ 02 ዲሽቃ፣ 02 ፓትሮል ሙሉ መሣሪያና ተተኳሽ።


፫. የጣና ገላውዴዎስ ክ/ጦር ግስጋሴ (ደራ)


በደራ ምድር ከአምበሳሜ እስከ ሐሙሲት፣ በተለይም "ግብጻዊት ማርያምና ገነት ወንዝ" አካባቢ በተደረገ ውጊያ የጠላት ኃይል ተደምስሷል። በውጊያው የጣና፣ አፈር ውኃ እና አምበሶ ብርጌዶች ጠላትን በመቁረጥ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅተዋል። 03 የአገዛዙ ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።


፬. የጋይንት ነፋስ መውጫ ነጻ መውጣት


በአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ እና በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተቀናጀ ኦፕሬሽን፣ የጋይንት ነፋስ መውጫ ከተማ በልጆቿ እጅ ገብታለች።


ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

 
 
 

Comments


bottom of page